Bank of Abyssinia @BoAEth 16.03.2026 18:11 Скопировать Пожаловаться "አሚን ለበጎነት" በሚል መሪ ሓሳብ እየተከናወነ የሚገኘው የረመዳን አስቤዛ የመለገስ መርሐ ግብራችን በጅማ ከተማም ቀጥሎ ውሏል። በዚህ የጅማ ዲስትሪክት ዳይሬክተር፣ የከተማው መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮችና የአቢሲንያ አሚን የብራንድ አምባሳደር በተገኙበት በተከናወነው የአስቤዛ ድጋፍ፤ ከ190 በላይ ወገኖቻችን ተጠቃሚ ሆነዋል። ከምንግዜውም በላቀ የኸይር ተግባራት በጉልህ በሚስተዋሉበት ታላቁ የረመዳን ወር፤ ባንካችን እየከወነው የሚገኘው ከወገኖቻችን ጋር በአብሮነት የመቆምና የኢፍጣር አስቤዛ የማቅረብ ተግባር በጅማ ዲስትሪክት ሥር በሚገኙት በመቱ፣ በአሶሳና በሜጢ ከተሞችም በቀሪዎቹ የረመዳን ቀናት ይከናወናል። "አሚን ለበጎነት" የተሰኘው መርሐ ግብር ባንካችን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በፆም ወቅት በቂ ማፍጠሪያ ማግኘት ለማይችሉ ወገኖቻችን የረመዳን አስቤዛ ድጋፍ የሚያደርግበት ሰፊ የኸይር ሥራ ዘመቻ መሆኑ ይታወቃል። ❤ 10 👍 5 1 15K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram