Bank of Abyssinia @BoAEth 12.03.2026 15:56 Скопировать Пожаловаться የታላቁ የረመዳን ወር የበጎነት ተግባራት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጉልህ የሚስተዋሉበት ጊዜ እንደመሆኑ፣ ባንካችን እየከወነው የሚገኘው ከወገኖቻችን ጋር በአብሮነት የመቆምና የኢፍጣር አስቤዛ የማቅረብ ተግባር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለበጎነት የተዘረጉት የአቢሲንያ አሚን እጆች እንደ ሁልጊዜውም በፆም ወቅት በቂ ማፍጠሪያ ማግኘት ለማይችሉና ለተቸገሩ ወገኖቹ በመድረስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህም በቢሾፍቱ ከተማ ከሚገኘው ኦሲስ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመቀናጀትና ድጋፍ በማድረግ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል። በመርሐ ግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የመጅሊስ አመራሮችና የባንካችን የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። አቢሲንያ አሚን በዚህ ታላቅ ወር የበጎነት አሻራውን በማሳረፍም ከተቸገሩ ወገኖቹ ጎን እንደሚቆም አስመስክሯል። አሚን ለበጎነት! #AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን ❤ 42 👍 10 🔥 3 😁 3 🤩 2 👌 1 2 20.6K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram