avatar
Bank of Abyssinia
@BoAEth
11.03.2026 16:56
አቢሲንያ ባንክ ከወለድ ነጻ አገልግሎት በሚሰጥበት አቢሲንያ አሚን በኩል በሚከውነው ‘አሚን ለበጎነት’ የረመዳን ድጋፍ መርሐ ግብሩ፤ ለወንድም ኻሊድ ፋውንዴሽን የረመዳን አስቤዛ ድጋፍና የአንድ ሚሊዮን ብር ሥጦታ አበረከተ።

የአቢሲንያ አሚን ዳይሬክተሮች፣ የዲስትሪክት አመራሮችና የብራንድ አምባሳደሩ ማዕከሉ የሚሰጠውን አገልግሎት ተዟዙረው የጎበኙ ሲሆን፤ ፋውንዴሽኑ በርካታ ቁጥር ያላቸውን እናቶችና ህፃናት፣ እንደዚሁም ወጣቶችና አረጋዊያንን በአንድ ጥላ ሥር በማቀፍና ዘርፈ ብዙ ሸክማቸውን በማቅለል ንቁና ምርታማ ዜጎችን ለማፍራት በማዕከሉ የሚከናወኑ ተግባራትን አድንቀዋል።
በመርሐ ግብሩ የአጋርነት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የወለድ ነፃ ቢዝነስ ሰርቪስ ዳይሬክተሩ አቶ አበጋዝ ይማም፤ ወርሐ ረመዳንን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ የሃሀራችን ከተሞች እየተከናወነ የሚገኘው የኢፍጣር አስቤዛና የገንዘብ ድጋፍ፤ የተራድኦ ተቋማቱ ለሚያከናውኑት የበጎነት ተግባር ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር ያለመ መሆኑን በመድረኩ ገልጸዋል። "አሚን ለበጎነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ዲስትሪክቶች በመከናወን ላይ የሚገኘው የባንካችን ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር፤ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ወገኖች ተጠቃሚ ማድረጉን ያወሱት ዳይሬክተሩ፤ በመጪዎቹ የረመዳን ቀሪ ቀናትም ይኸው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የአቢሲንያ አሚን የብራንድ አምባሳደር ሙሐመድ ፈረጅ፤ ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በትምህርት፣ በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የፈጠራ አቅም ያላቸው ወጣቶች ላይ እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አሚን ለበጎነት!

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን
👍 19
13
👏 4
2 16.3K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Bank of Abyssinia

186.2K
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Открыть в Telegram