avatar
Bank of Abyssinia
@BoAEth
09.03.2026 16:26
አቢሲንያ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን በሚሰጥበት አቢሲንያ አሚን በኩል፤ በያዝነው የረመዳን ወር እየከወናቸው የሚገኙ የበጎነት ተግባራት ቀጥለዋል።

"አሚን ለበጎነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ከተሞችና ተቋማት እየተደረገ የሚገኘው የአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የረመዳን አስቤዛ የማድረስ ተግባር፤ በትላንትናው ዕለት በአንጋፋው አወሊያ ትምህርት ቤት ተከናውኗል። የአቢሲንያ አሚን የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የአቢሲንያ አሚን የብራንድ አምባሳደሩ በተገኙበት የተከናወነው የአስቤዛ ስጦታ፤ በኑሯቸው አቅመ ደካማ ለሆኑ አረጋዊያን፣ ለወላጅ አጥ ህፃናትና ጧሪ ለሌላቸው እናቶች የተበረከተ ነበር።

የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ እየተከናወነ የሚገኘውን ወገንን የማገዝና ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር በማድነቅ፤ የባንኩን የድጋፍና እገዛ ሥራዎች ያመሰገኑት የአወሊያ እርዳታና ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሐጅ ሰዒድ አስማረ፤ አቢሲንያ አሚን ከረመዳን አስቤዛ ድጋፍ በተጨማሪ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ተማሪዎች "በአሚን ስኩል አዋርድ" የሚሸልመው ማበረታቻና ለውጤታማ መምህራን የሚሰጠው የማትጊያ ሽልማት ሰፊ ትርጉም የሚሰጠው ተግባር መሆኑን አውስተዋል። "አሚን ለበጎነት" በሚል መሪ ሐሳብ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየተተገበረ የሚገኘው የባንካችን የረመዳን እንቅስቃሴ በቀጣዮቹ ቀናትም እንደሚቀጥል በባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመድረኩ ተጠቅሷል።


#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን
96
👍 15
👌 4
😱 2
🔥 1
3 20.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Bank of Abyssinia

186.2K
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Открыть в Telegram