avatar
Bank of Abyssinia
@BoAEth
09.03.2026 11:35
"አሚን ለበጎነት" የረመዳን አስቤዛ ድጋፍ በድሬዳዋ ከተማ ተከናወነ!

አቢሲንያ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን በሚሰጥበት አቢሲንያ አሚን በኩል እየተከናወነ የሚገኘው የረመዳን አስቤዛ ድጋፍ፤ እሁድ የካቲት 29/2018 በድሬዳዋ ከተማ ተከናወነ።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሐር፣ የአስተዳደሩ የብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር ኢብራሒም ዩሱፍ እና የአቢሲንያ ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር፣ የአቢሲንያ አሚን የሥራ ኃላፊዎች እና የብራንድ አምባሳደሩ በተገኙበት የተካሄደው የረመዳን አስቤዛ ድጋፍ ተግባር፤ ከሸይኽ በክሪ ሰበሎ ፋውንዴሽን ጋር በመቀናጀት የተከናወነ ነው።

አቢሲንያ አሚን ለወገን ድጋፍ ማድረጉንና ማኅበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን በማድነቅ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ክቡር ከንቲባው፤ የባንኩ ወገንን የማገዝ ተግባር የመሰል ተቋማት ቀዳሚ ኃላፊነት መሆኑን በማውሳት ለወደፊቱም ማኅበረሰብ አቀፍ ሥራዎች ላይ ያለው የባንኩ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አቢሲንያ አሚን በወርሐ ረመዳን እየከወነው የሚገኘው የበጎነት ተግባር በርካታ ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረጉን የገለጹት የድሬዳዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ በቀለ፤ የባንካችን አንድ እሴት የሆነው ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባር በተለያዩ ከተሞችና ተቋማት መቀጠሉን ገልጸው፤ በድሬዳዋ ከተማ ከሁሉም ቀበሌዎች ለተውጣጡ አቅመ ደካማ ወገኖቻችን የተደረገው መሰረታዊ የአስቤዛ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን
37
😱 3
👌 3
🤩 2
👍 1
7 20.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Bank of Abyssinia

186.2K
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Открыть в Telegram