Bank of Abyssinia @BoAEth 07.03.2026 13:10 Скопировать Пожаловаться "አሚን ለበጎነት" በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ከተሞችና ተቋማት እየተደረገ የሚገኘው የአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የረመዳን አስቤዛ የማድረስ ተግባር ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። በዚህም በዛሬው ዕለት በአብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም የዓይነ ሥውራን አዳሪ የቁርኣን ት/ቤት የአቢሲንያ አሚን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ሸይኽ ኑረዲን ደሊል፣ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የአቢሲንያ አሚን የብራንድ አምባሳደር በተገኙበት የረመዳን አስቤዛ ለተማሪዎች ማድረስ ተችሏል። ድጋፉን በማስመልከት ምስጋናቸውን ያቀረቡት የአብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም የዓይነ ሥውራን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ ኢብራሒም ሰዒድ፤ የአቢሲንያ አሚንን ድጋፍ በማድነቅና ከዚህ ቀደም ባንኩ ሲያደርግላቸው የነበረውን የተለያየ እገዛ በማውሳት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። #AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #አቢሲንያአሚን ❤ 48 👍 13 👌 6 🔥 3 3 21.8K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram